እምነት ከታጠቀ
Emnet Yetateqe
2004 · ትራክ 5 · 4:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እምነት ከታጠቀ አምላኩን ከጠራ
አማኝ ድል አይሆንም በእሳት በመከራ
እምነት የሁሉም መሠረት (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተጠራጣሪ ሰው ጌታን ያኮሰሰ
በጠላት ተማርኮ ተረቶ አለቀሰ (፪x)
በእምነት ግን የገባ የጠላቱን መንደር
አሸንፎ ሳቀ የጌታ ወታደር
አዝማች · Chorus
እምነት ከታጠቀ አምላኩን ከጠራ
አማኝ ድል አይሆንም በእሳት በመከራ
እምነት የሁሉም መሠረት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ታምኖ የወጣ ሰው የእምነት ችቦ አንድዶ
ጠላቱን አጠፋ ኢያርኮን ንዶ (፪x)
አምላኩን ፈትኖ እምነት ከታጠቀ
በተረከዙ ጫፍ ባህር አደረቀ
አዝማች · Chorus
እምነት ከታጠቀ አምላኩን ከጠራ
አማኝ ድል አይሆንም በእሳት በመከራ
እምነት የሁሉም መሠረት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በፊቱ ቢጋረድ ተስፋ ሲያስቆርጠው
የእምነት ዘንግ አንስቶ ባሕሩን ከፈለው (፪x)
በድል ተሻገረ የእምነት ካባ አጥልቆ
ዳግም ላይደርስበት ከጠላቱ ርቆ
አዝማች · Chorus
እምነት ከታጠቀ አምላኩን ከጠራ
አማኝ ድል አይሆንም በእሳት በመከራ
እምነት የሁሉም መሠረት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ