የአንበሳን አፍ የዘጋ
Yeanbesan Af Yezega
2004 · ትራክ 10 · 5:25 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የአንበሳን አፍ የዘጋ ጠላቴንም የወጋ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከትውልዱ ወሰን እኩያ የሌለው
ፊተኛው ኋለኛው ዘላለም የሆነው
የዕውቀት ማህደር የሰላም አለቃ
ኢየሱስ ለእኔ የነፍሴ ጠበቃ
አዝማች · Chorus
የአንበሳን አፍ የዘጋ ጠላቴንም የወጋ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍርሃትን ከቦ ችግር ሲጋርደኝ
አንበሳው አፍጦ ሊገለባብጠኝ
ደረሰ ጌታዬ የአማልክቶች አምላክ
ይኸው ነፃ ወጣሁ አምልኬ ይባረክ
አዝማች · Chorus
የአንበሳን አፍ የዘጋ ጠላቴንም የወጋ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዘመን የማይሸረው የዘመናት ጌታ
ሞትንም ድል ነስቶ ሲኦልን የረታ
ኃያል የሆነ ድንቅ ምርኮን የሚያመጣ
ለእኔ ጌታ ኢየሱስ አቻ ከየት መጣ
አዝማች · Chorus
የአንበሳን አፍ የዘጋ ጠላቴንም የወጋ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ፍሙን አጋግሎ አሳቱን አንድዶ
ሊያጠፋኝ ሲፈልግ ያ ቸካኙ ዘንዶ
ቃል ኪዳን የገባው ደረሰ ጌታዬ
በረታሁ ደስ አለኝ ተድሶ ተስፋዬ
አዝማች · Chorus
የአንበሳን አፍ የዘጋ ጠላቴንም የወጋ
የእኔ ጌታ ኢየሱስ አልፋና ኦሜጋ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ