መቃብሩን ፈነቃቀለው
Meqaberun Feneqaqelew
2004 · ትራክ 3 · 6:05 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መቃብር ሊያዘው አልቻለም
ጌታችን ተቀብሮ አልቀረም
ጐልጐታ ላይ ሞቶ የነበረው
መቅብሩን ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከሙታን መካከል ሕያውን
የምትፈልጉት አረ ለምን
እዚህ የለም ኢየሱስ ተነስቷል
መቃብሩን ባዶ አድርጐታል
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወታደር ሲጠብቅ የቄሳር
ኢየሱስን ሊያስቀር መቃብር
ከኃይል ሁሉ በላይ ኃይል ያለው
መቃብሩን ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ሰው የሞተው ያ ጌታ
በድካሙ ጠላት የረታ
የሞትንም ጉልበት ሰባብሮ
ድል አድርጓል ማህተሙን ሽሮ
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
መድኃኒት ከጽዮን የወጣ
ሊያድነን ከሰማይ የመጣ
ሞትን ለዘለዓለም የሻረው
መቃብሩን ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
መቃብሩን ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) የይሁዳ አንበሳ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ