ደጅ እጠናለሁ
Dej Etenalehu
2004 · ትራክ 11 · 4:33 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ እስከምታየኝ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም አልሄድም ደጅ ጠናለሁኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ካህኑ ኤሊ እንኳን ምንም ባይረዳት
እንደምናምንቴ ሰካራም ቢቆጥራት
ሃና በአንተ ፊት እንባዋን ስታፈስ
ሳሙኤልን ሰጠሃት የልመናዋ መልስ
አዝማች · Chorus
አንተ እስከምታየኝ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም አልሄድም ደጅ ጠናለሁኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምድረበዳ ውስጥ ብቻዋን እያለች
አጋርን የሚያያትን በዓይኖቿ አየች
እኔም ዝም ብዬ አንተን ጠብቃለሁ
በረሃውም ምንጭን ሲያፈልቅ አየዋለሁ
አዝማች · Chorus
አንተ እስከምታየኝ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም አልሄድም ደጅ ጠናለሁኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ማንም ባይረዳ የልቤን የውስጥ ችግር
ጀሮ ዳባ ቢሉኝ ልናገር ስሞክር
ልታስወግድ የለም ፊቴም በእንባ ይራስ
የአንተ ጊዜ ደርሶ እስክታሰብ ድረስ
አዝማች · Chorus
አንተ እስከምታየኝ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም አልሄድም ደጅ ጠናለሁኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ያየሁት ራዕይ በልጅነት ወራት
የማይሞላ ቢመስል ቢያስቆጥር ዓመታት
የአንተ ጊዜ ሲደርስ ንጉሥ ያስኩቸኩላል
የመከራው ዘመን በክብር ይተካል
አዝማች · Chorus
አንተ እስከምታየኝ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም አልሄድም ደጅ ጠናለሁኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ