Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የኢየሱስ ሥም

Yeyesus Sem

2004 · ትራክ 9 · 4:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከጠላቴ ጋራ ስሟገት

ነፍሴም አታ ሳለ እረፍት

ወደ ተራሮችም አየሁ

እረዳት ግን ምንም አጣሁ

ግን መድሃኒቴን ስጠራው

ሲበራ አየሁ የድል ጮራው

የኢየሱስ ሥም ኃይል ነው

የኢየሱስ ሥም ጉልበት ነው

የኢየሱስ ሥም ፈውስ ነው

የኢየሱስ ሥም ከሥሞች በላይ ነው (፪x)

አልናድ ያለው ተራራ

ተናደ የሱን ሰም ስጠራ

አልሞላ ያለ ሸለቆ

ታየኝ በጌታዬ ሞልቶ

በታምራቱ አስደነቀኝ

የስሙን ኃይል አሳየኝ

የኢየሱስ ሥም ኃይል ነው

የኢየሱስ ሥም ጉልበት ነው

የኢየሱስ ሥም ፈውስ ነው

የኢየሱስ ሥም ከሥሞች በላይ ነው (፪x)

ሞቴን በሞቱ የሻረው

ስሞ መድሃኒቴ የሆነው

እስከ ዛሬም አልተረታ

ዘላለም የማይረታ

ለእርሱ ልዘምር በደስታ

ይክበር እያልኩ በዕልልታ

የኢየሱስ ሥም ኃይል ነው

የኢየሱስ ሥም ጉልበት ነው

የኢየሱስ ሥም ፈውስ ነው

የኢየሱስ ሥም ከሥሞች በላይ ነው (፪x)

እያሪኮ ቢሆን ጐልያድ

በፊታችሁ ቢገደገድ

የኢየሱስን ሥም ስንጠራ

ይወድቃሉ በየተራ

ከሥሞች በላይ ሥም ያለው

የእግዚአብሔር ልጅ ታላቅ ነው

የኢየሱስ ሥም ኃይል ነው

የኢየሱስ ሥም ጉልበት ነው

የኢየሱስ ሥም ፈውስ ነው

የኢየሱስ ሥም ከሥሞች በላይ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ