ኢየሩሳሌም
Eyerusaliem
2004 · ትራክ 12 · 5:34 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳን
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የናፈቀኝ ዜማ የቅዱስ ዝማሬ (፪x)
አልቀርም ሳልዘምር ከጻድቃን አብሬ
ከበጉ ዙፋን ሥር ሳልዞር በደስታ (፪x)
አልቀርም ሳላይሽ አንች ቅዱስ ቦታ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳን
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማቋረጫው መንገድ ሊጠልፈኝ ቢነሳ (፪x)
ሳላየው አልቀርም የይሁድን አንበሳ
ብቻዬን ብቀርም መንገደኛው ሸሽቶ (፪x)
ሳልዘምር አልቀርም ኢየሱሴ መጥቶ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳን
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የመናይ ተራራ መቧጠጥ ቢያቅተኝ (፪x)
የበረሃው ጉዞ ውኃ ጥም ቢጐዳኝ
የሚያረካው ጌታ ሲመታ ከሰማይ (፪x)
ይረዳኛል በርግጥ ያቺን ቦታ እንዳይ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳን
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ