Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ባለውለታዬ ነው

Gieta Baleweletayie New

2004 · ትራክ 1 · 6:56 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ብዙ (፫x) ምሥጋና አለኝ ለአምላኬ የምሰጠው

ብዙ (፫x) ዝማሬ አለኝ ለእርሱ የምዘምረው (፪x)

ጌታ እርሱ ባለ ውለታዬ ነው (፬x)

ነፍሴ ሆይ ተነሽ ጌታ እግዚአብሔርን ባርኪ

ዙሪያሽ በሚሆነው ከቶ አትታወኪ

የሁሉ የበላይ ገዢ አምላክ ነውና

በእርሱ ደስ ይበልሽ ሰዊለት ምሥጋና (፪x)

ብዙ (፫x) ምሥጋና አለኝ ለአምላኬ የምሰጠው

ብዙ (፫x) ዝማሬ አለኝ ለእርሱ የምዘምረው (፪x)

ጌታ እርሱ ባለ ውለታዬ ነው (፬x)

በገናም ይነሳ እኔም ማልጄ እነሳለሁ

ለወደደኝ ለእርሱ ቅኔ እቀኛለሁ

አፌን በምሥጋና በቅኔ ለሞላው

የምለው የለኝም ከምሥጋና ሌላ (፪x)

ብዙ (፫x) ምሥጋና አለኝ ለአምላኬ የምሰጠው

ብዙ (፫x) ዝማሬ አለኝ ለእርሱ የምዘምረው (፪x)

ጌታ እርሱ ባለ ውለታዬ ነው (፬x)

የኢየሱስን ማዳን ነፍሴ እጅግ ተውቀዋለች

የመስቀሉን ፍቅር አይታ ተማርካለች

ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ድንቅ ብርሃን

አውጥቶኛልና ልሰዋ ምሥጋና (፪x)

ብዙ (፫x) ምሥጋና አለኝ ለአምላኬ የምሰጠው

ብዙ (፫x) ዝማሬ አለኝ ለእርሱ የምዘምረው (፪x)

ጌታ እርሱ ባለ ውለታዬ ነው (፬x)

ክብሩ ሰማያትን ምድርን ሁሉ የሸፈነ

ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሥሙ የገነነ

አምላካዊ ክብሩን ትቶ የፈለገኝ

ልሰዋ ምሥጋና በዝማሬ ልቀኝ (፪x)

ብዙ (፫x) ምሥጋና አለኝ ለአምላኬ የምሰጠው

ብዙ (፫x) ዝማሬ አለኝ ለእርሱ የምዘምረው (፪x)

ጌታ እርሱ ባለ ውለታዬ ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ