አትተወኝ
Atetewegn
2010 · ትራክ 10 · 4:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምክንያት : አላቀርብም : ለኃጢአቴ
ራሴን : አውቀዋለሁ : ማንነቴን
አንተ : ግን : ጻጽቅ : ነህ : ለዘለዓለም
ታውቀኛለህና : የትም : አልሄድም
አሳዝኜሃለሁ : እውነት : ነው
አላስከበርኩህም : አውቃለሁ
አዝማች · Chorus
ነገር : ግን : ጌታ : ሆይ : ማረኝ : እላለሁ
ምህረትህ : ብዙ : ነው : አንጻኝ : ነጻለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፊትህ : አትጣለኝ : ከቶ : ዝም : አትበለኝ
ቅዱሱን : መንፈስህን : ከ : እኔ : አትውሰድብኝ
መለወጥ : እሻለሁ : ከ : ኃጢአቴ : አንጻኝ
በደምህ : እጠበኝ : እኔም : እነጻለሁኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃጢአተኝነቴ : እጅግ : አሳዝኖህ
ትተኸኝ : እንዳትሄድ : ለፈቃዴ : ሰጥተህ
እኔ : ባሳዝንህም : አትተወኝ : እባክህ
መሃሪ : ነህና : በ : እጅህ : ላይ : ጣለኝ
አሳዝኜሃለሁ : እውነት : ነው
አላስከበርኩህም : አውቃለሁ
አዝማች · Chorus
ነገር : ግን : ጌታ : ሆይ : ማረኝ : እላለሁ
ምህረትህ : ብዙ : ነው : አንጻኝ : ነጻለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ኃጢአተኛን : ትተህ : ጨክነህ : ብትሄድ
ማን : ይመልሰዋል : ከሲዖል : መንገድ
እኔም : ወደ : ሲዖል : ብሄድ : ማን : ያድነኛል
በእጅህ : ላይ : መጣል : እርሱ : ይሻለኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ