ናፍቃለሁ
Nafeqalehu
2010 · ትራክ 1 · 5:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃያላን ሲነሱ እርስ በዕርሳቸው
ምድር ስትናወጥ ግራ ሲገባቸው
ቀኑ ሲደርስ ግን አንተ ስትመጣ
ያን ጊዜ ያበቃል የዚች ዓለም ጣጣ
አዝማች · Chorus
ናፍቃለሁ ያንን ቀን ላይ ሁልጊዜ እሮጣለሁ
የተሰቀለውን የሞተውን የተነሳውን ላየው
የመላዕክት ድምፅ ዝማሬያቸው ከሩቁ ይሰማኛል
የምጠብቀው ጌታ ኢየሱስ መምጫው ጊዜ ደርሷል
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉ በሁሉ ነው ምንም አይጐድለንም
በሰማይ ቤት ስቃይ ጉስቁልና የለም
እንዘምራለን ዘለዓለም በደስታ
ለይሁዳ አንበሳ ሞትን ድል ለነሳ
አዝማች · Chorus
ናፍቃለሁ ያንን ቀን ላይ ሁልጊዜ እሮጣለሁ
የተሰቀለውን የሞተውን የተነሳውን ላየው
የመላዕክት ድምፅ ዝማሬያቸው ከሩቁ ይሰማኛል
የምጠብቀው ጌታ ኢየሱስ መምጫው ጊዜ ደርሷል
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ሲመጣ በመላእክት ታጅበን
ከሙሽራው ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለህ
የሚያሰጋን የለም ዕዳችን ሁሉ ተከፍሏል
በነጽነት ልንኖር ከእርሱ ጋር
ዳግመኛ በክብር ይመጣል (፪x)
ጌታ ሲመጣ በመላእክት ታጅበን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ