እጠብቅሃለሁ
Etebeqehalehu
2010 · ትራክ 8 · 5:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰምቼ ነበረ ስታንኳኳ በሬን
ግን አላስተዋልኩም አንተ መሆንህን
ብዙ አድክሜሃለሁ አውቃልሁ እራሴ
ግን እራርተህልኝ ቤቴ ትመጣ ይሆን
አዝማች · Chorus
እጠብቅሃለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ
በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ
ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፅናና
ቁጥር 2 · Verse 2
ግን አንተ ዝም ካልከኝ እፈራለሁና
ዝም ስትል ጊዜ ስታጠፋ ድምጽህን
ያሰብኩት በሙሉ እንዳልነበር ሲሆን
ቀኑ ሲጨላልም ፈርቼ ይህን ሁኔታ
መልዕክት ልኬ ነበር ትመጣ ይሆን የሚል
አዝማች · Chorus
እጠብቅሃለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ
በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ
ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፅናና
ቁጥር 3 · Verse 3
ግን አንተ ዝም ካልከኝ እጠፋለሁና
እንግዳዬ ኢየሱስ እረፍ ቤቴ ገብተህ
ብዙ የምነግርህ አለኝ ማጫውትህ
ልቤ አንተ ቤት ነው ሀሳብህን ፈፅም
እጠብቅሃለሁ ከቶ አልሰለችም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ