ከአድማስ ባሻገር
Keadmas Bashager
2010 · ትራክ 5 · 4:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአድማስ ባሻገር ከዓይናችን የራቀ
ከሩቁ ስናየው ሰማዩ ወደቀ
ነገር ግን የአራቱም መጨረሻ አንተ ነህ
ፍጥረት እጅህ ላይ ነው ምን ያህል ትልቅ ነህ
አዝማች · Chorus
በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ
ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ
ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ
ክብር ለሥምህ ይሁን
ቁጥር 2 · Verse 2
ንፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል
የበረዶው ክምር ማን አጥቦ አፅድቶታል
ምድርን ስትሰራ ማን ነበረ አብሮህ
እንዲህ አድርግ ብሎህ ማንስ አማከረህ
አዝማች · Chorus
በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ
ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ
ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ
ክብር ለሥምህ ይሁን
ቁጥር 3 · Verse 3
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑህ
እልፍ እእላፍ መላእክቶች ወድቀው የሚሰግዱልህ
በእውነት አንተ እግዚአብሔር ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ
ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ
ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ
ክብር ለሥምህ ይሁን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ