ሁኔታዎችን
Hunietawochin
2010 · ትራክ 7 · አማርኛ
መግቢያ · Intro
ሁኔታዎችን አይቼ ተመስገን አልልህም
ያሰብኩት ባይሳካ አፌን አላበላሽም
እግዚአብሔር አንተ በእውነት ጻድቅ ነህ
የሚሳንህ አንዳች የለም
ይሆናል አይሆን ብዬ በዚህ አልገመግምህም
ቁጥር 1 · Verse 1
ለባህር ገደብን ሰጠህ
ከዚህ አትለፍ ብለህ
ፀሀይም በማለዳ በቃልህ ያጸና
አንተ ስትናገር የማይሆን የቱ ነው
ሁኔታን አይቼ ክፉ አይወጣኝም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ለእኔ ያለህ አላማ መልካም ነው ለዘለዓለም
በሞት ጥላ ውስጥ ብራመድ ክፉውን እኔ አልፈራም
ብታድነኝ ባታድነኝም ብትሰጠኝ ብትነሳኝም
አምልኮ ስራዬ እንጂ የሕይወቴ ጊዜያዊው ስሜት አይደለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በስራህ አትሳሳትም
አማካሪ አትፈልግ የትኛው ነገር አቅቶህ
ስለዚህ ራሴን እንቃለው በምትሰራው ስራ
ምህረትህ ለእኔ ይብዛልኝ
ለሃጥያቴ ከማውቅህ በላይ ነህና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ