ዘለዓለም አይጠፋም
Zelalem Aytefam
2010 · ትራክ 9 · 5:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሥራህን ለመግለፅ አንደበት ቢያንሰኝም
ከምሥጋና በቀር የምለው የለኝም
ሳወራው እኖራለሁ እስከ ለዘለዓለም
ያደረከው ሁሉ ከልቤ አይጠፋም
ጊዜው ቢርቅ ብዙ ቢያልፍም
ከልቤ ውስጥ ከቶ አይጠፋም
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ትዝ ይለኛል እስከ ዘለዓለም
አዝማች · Chorus
ዘለዓለም አይጠፋም ኢየሱስ ፍቅርህ
ያደረከው ሁሉ ዉለታህ
ከቶ አልረሳውም ታትሟል በልቤ
የዘለዓለም ፍቅሬ ነህ ወዳጄ
ቁጥር 2 · Verse 2
መገረፍ መድማትህ ለእኔ መሞትህ
ከጥፋት እንዳመልጥ ከክብርህ መውረድህ
ከተወጋው ጐንህ የፈሰሰው ደምህ
ዘወትር ትዝ ይለእኛል ኢየሱስ መከራህ
የመስቀሉ ዉለታህ ለእኔ ትልቅ ትዝታ ነው መድህኔ
ሕይወትን ሰጥተህ አድነኀኛል
ፍቅርህ ከልቤ ወስጥ እንዴት ይጠፋል
አዝማች · Chorus
ዘለዓለም አይጠፋም ኢየሱስ ፍቅርህ
ያደረከው ሁሉ ዉለታህ
ከቶ አልረሳውም ታትሟል በልቤ
የዘለዓለም ፍቅሬ ነህ ወዳጄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓይኔ ሌላ ከቶ አያይም
ምርጫዬ ነህ ለዘለዓለም
ፍቅርህ ልቤን ውስጥ ሰርጾ ገብቷል
ማንም ሳይቀይረው ይኖራል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ