ለሥምህ
Lesemeh
2010 · ትራክ 4 · 5:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትዝ ይለኛል የማልረሳው ብዙ ታሪክ አለኝ
ራሴን አውቃለሁ ማንነቴን ከየት እንዳነሳኝ
ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሰው ያለፈውን ሁሉ
ስታግዘኝ ያዩ ዓይኖቼ በእንባ ይሞላሉ
አዝማች · Chorus
ክብር ለሥምህ ይሁን እዚህ አደረስከኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ቀን ይመሻል ደግሞ ይነጋል
ሁሉም ነገር ያልፋል
ትዝታውን ግን ለመርሳት ከቶ እንዴት ይቻላል
ቁጥር 3 · Verse 3
ባትደርስልኝ ባትዘረጋው የምህረት እጅህን
ሳስበው እፈራለሁ መጨረሻዬን
አዝማች · Chorus
ክብር ለሥምህ ይሁን እዚህ አደረስከኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
በደስታ በሀዘኔ ከቶ ሳትለየኝ
ተሸከምከኝ እዚህ አደረስከኝ
ቀኖቹ ቢያልፉ መቼም አይረሳኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ዛሬ ቆሜ ዘምረዋለሁ ለእኔ ያደረከው ብዙ ነው
አንዳች የለም ከእኔ ነው የምለው
አመሰግንሃለሁ
ሁሉም አልፎ ዛሬ ቆሜያለሁ
ከአንተ የተነሳ እዚህ አለሁ
ስለነገ እንዴት እፈራለሁ
ሕይወቴ በእጅህ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ