ቀን
Qen
2010 · ትራክ 12 · 4:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ድግስ አዘጋጅቷል ንጉሡ በይፋ
ያላወቀ ሁሉ በከንቱ እንዳይለፋ
ለሚገባው ሁሉ በእውነተኛው በር
መንገዱ አንድ ነው የለም ከእርሱ በቀር
ልብሳችንን አጥበን አጽድተን በደሙ
ተግተን እንጠብቀው ቅርብ ነው ሰዓቱ
አዝማች · Chorus
አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሚያየኝን ጌታ እኔ አየዋለሁ
በደስታ ሁሌ በፊቱ እዘምራለሁ
ዘለዓለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ
እንዴት ግሩም ቀን ነው ጌታን የማይበት
ከዚህች ዓለም ስቃይ ከቶ የማርፍበት
ኢየሱስ ይመጣል ታጅቦ በክብር
አብረን እንሄዳለን ልንኖር ከእርሱ ጋር
አዝማች · Chorus
አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሚያየኝን ጌታ በዐይኔ አየዋለሁ
ከደመና ከፍ ካለው በላይ እሄዳለው
ዘለዓለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ
እንዴት ብሩህ ቀን ነው ያን ቀን
አብረን እንሄዳለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ