በምህረቱ
Bemeheretu
2010 · ትራክ 11 · 5:25 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃጥያተኛ ነበርኩ ዓለም ጉድ ያለልኝ
ለሰራሁት በደል ሞት የፈረዱብኝ
ገበናዬን ገልጠው እየገፈተሩኝ
ለፍርድ አቀረቡኝ በድንጋይ ሊወግሩኝ
ዳኛው ግን ስለ እኔ በእውነት አዘነልኝ
ውስጡን እያወቀ ለእኔ ፈረደልኝ
ከከሳሾቼ እጅ በጥበብ አስጥሎኝ
በእኔ ፋንታ እርሱ ሞቶ ከፈለልኝ
አዝማች · Chorus
በምህረቱ ዛሬ ቆሜያለሁ
ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ
ነፍሴን ከሚሹ ከከሳሾቼ
ማምለጥ ችያለሁ ምህረት አግኝቼ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ
የምህረቱ ብዛት ከባሕር ይጠልቃል
ስለኀጢያተኛው በእውነት ግድ ይለዋል
እርሱ ነው ዳኛዬ የሆነኝ ጠበቃ
ቀድሞ የታደገኝ ሕይወቴ ሲያበቃ
ከሳሾቼ ሁሉ ድንጋያቸውን ጥለው
ወደ ኋላ ሸሹ ህሊና ወቅሷቸው
ስራዬን ሰርቶታል አሁን ነጻ ሰው ነኝ
ላዳነኝ ኢየሱስ እዘምራለሁኝ
አዝማች · Chorus
በምህረቱ ዛሬ ቆሜያለሁ
ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ
ነፍሴን ከሚሹ ከከሳሾቼ
ማምለጥ ችያለሁ ምህረት አግኝቼ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዋጋዬ ይሄ ነው
በእርሱ ደም ታጥቤያለሁ እኔ ድኛለሁ
ስለ እኔ ሞቶ አድኖኛል
በእርሱ ቁስል ተፌውሻለሁ
ነፍሴን ከሚሹ ከአዳኝ ወጥመድ
አስመለጠኝ አኔን አዳነኝ
ዛሬ በደስታ ዘምራለሁ
በእርሱ ቁስል እኔ ድኛለሁ
ፍቅሩን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ
ከሞት አፍ ከጫፍ ላይ አውጥቶኛልና
ታሪኬን አወራለሁ
ምህረቱን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ
ለነፍሴ መዳን ሆኖላታልና
ሥሙን እባርካለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ