ጌታ ሆይ
Gieta Hoy
2010 · ትራክ 2 · 3:55 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሽክሜን እና ጭንቀቴን
በፊትህ ይዤ እቀርባለሁ
ያለፈው ይበቃኛል
መለወጥን እሻለሁ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የልመናዬን ቃል ስማ
ፀሎቴንም መልስልኝ እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ
በእራሴ ብዙ ደክሜያለሁ ስለፋ
ቁጥር 2 · Verse 2
የማላውቀውን ተስፋ ዕድሜዬን ሙሉ ስለፋ
የአንተን የልብህን ሃሳብ እየፈጸምኩኝ መኖር እሻለሁ
ከዚህች ዓለም ከንቱ ነገር ዐይኔንም አነሳዋለሁ
ዋጋ አለውና የከበረ እርሱን ለመያዝ እዘረጋለሁ
ከእንግዲህ በቀረኝ እድሜ ክብርህን ማየት እሻለሁ
ባለማስተዋል የሰበሰብኩት
ከንቱ ብቻ ነው ለካስ ያከማቸሁት
ክፋቴን ሁሉ ዞር ብዬ ሳየው
እራሴን ስወቅስ ደግሞ እገኛለሁ
ደግሞ እንደገና ነግቶልኝ ስሮጥ
አንድ ዐይነት ሕይወት የማይለወጥ
ይህ ከንቱ ኑሮ ብዙ ደከመኝ
አሁን ግን በቃኝ ባክህ ለውጠኝ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የልመናዬን ቃል ስማ
ፀሎቴንም መልስልኝ እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ
በእራሴ ብዙ ደክሜያለሁ ስለፋ
ቁጥር 3 · Verse 3
የማላውቀውን በተስፋ ዕድሜዬን ሙሉ ስለፋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ