ባርነትን ሸሽተው የወጡት
Bareneten Sheshtew Yewetut
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የባርነት ኑሮ ሰልችቷቸው ተመረዉ
ቅድስቲቷን ከተማ ተመኝተው ፈልገዋት
ተጨንቀህ ተጠበህ ያወጣሃቸው ምርጥህ ሕዝቦች
የት ሄደው አለቁ ጌታዬ ደምህ ፍሬዎች
አዝማች · Chorus
ባርነትን ሸሽተው ከግብጽ ምድር የወጡት
የት ሄደው አለቁ ከነአንን ሳያይዋት
ጌታ መልሳቸው ወደ መንጐችህ በረት
በሩ ሳይዘጋ ሳይደርስባቸው የፍርድ እለት
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲያለቅሱ በምኞት እጅግ ናፍቀው ያቺን ሃገር
ደግሞም እየጠጡ የሕይወትን ውኃ በፍቅር
ጸጋር በዝቶላቸው የነበሩት በአገልግሎት
ምን ጠቃሚ አገኙና ጥለውህ ሄዱ ከአንተ ሚበልጥ
አዝማች · Chorus
ባርነትን ሸሽተው ከግብጽ ምድር የወጡት
የት ሄደው አለቁ ከነአንን ሳያይዋት
ጌታ መልሳቸው ወደ መንጐችህ በረት
በሩ ሳይዘጋ ሳይደርስባቸው የፍርድ እለት
ቁጥር 3 · Verse 3
በምህረትህ አቅፈህ አሳድገህ በአንተ ጉያ
እንዴት ይችሉታል የበረሃውን መሰማሪያ
የሕይወቱን ውኃ እየጠጡ ያደጉትን
እንዴት ይችሉታል የበረሃውን ጥማትን
አዝማች · Chorus
ባርነትን ሸሽተው ከግብጽ ምድር የወጡት
የት ሄደው አለቁ ከነአንን ሳያይዋት
ጌታ መልሳቸው ወደ መንጐችህ በረት
በሩ ሳይዘጋ ሳይደርስባቸው የፍርድ እለት
ቁጥር 4 · Verse 4
የደምህን ፍሬ ዘርተህ ነበር በጭንቅ ጌታ
አድገዋል ሲባሉ ጠወለጉና ጠፉ ጌታ
ኧረ መልሳቸው ጌታ ኢየሱስ ስለደምህ
ወደ ለምለም ይምጡ ከበረሃው ግልገሎችህ
አዝማች · Chorus
ባርነትን ሸሽተው ከግብጽ ምድር የወጡት
የት ሄደው አለቁ ከነአንን ሳያይዋት
ጌታ መልሳቸው ወደ መንጐችህ በረት
በሩ ሳይዘጋ ሳይደርስባቸው የፍርድ እለት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ