እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
Eneho Yealemen Hatiyat Yemiyasweged
2011 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለሰው ሁሉ የሚያበራው
እውነተኛው የዓለም ብርሃን
በዓለም ውስጥ የነበረው
ዓለሙ ግን ያላወቀው
አዝማች · Chorus
እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
ዮሐንስ የመሰከረለት የእግዚአብሔር በግ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙም ለሚያምኑም
የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ
ስልጣንንም ሰጣቸው
አዝማች · Chorus
እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
ዮሐንስ የመሰከረለት የእግዚአብሔር በግ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እውነትን ተሞልቶ በእኛ ውስጥ ያደረ
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ የከበረ
እግዚአብሔርን የለም ያየው
በአባቱ እቅፍ ያለው ግን ተረከው
አዝማች · Chorus
እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
ዮሐንስ የመሰከረለት የእግዚአብሔር በግ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ