በተከበበች ከተማ
Betekebebech Ketema
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በተከበበች ከተማ የሚያስደንቀውን ምህረቱን
በእኔ ላይ የገለጠው እግዚአብሔር ይመስገን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ደመናም ውኃም ባላይ ሸለቆውን የሚሞላ
በእርሱ እታመናለሁ በክንዶቹ ጥላ
ጌታን ተስፋ አድርገው የሚጠባበቁ
እንዳይጠፉ አውቃለሁ ከቶም እንዳይወድቁ
አዝማች · Chorus
በተከበበች ከተማ የሚያስደንቀውን ምህረቱን
በእኔ ላይ የገለጠው እግዚአብሔር ይመስገን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰማያት ተናውጠው በክብሩ ይወርዳል
የልጆቹ ነገር ጌታ ግድ ይለዋል
ታምኜ እቆማለሁ በዓለቱ ላይ
በፍጽሜው ዘመን ዐይኖቹን እስካይ
አዝማች · Chorus
በተከበበች ከተማ የሚያስደንቀውን ምህረቱን
በእኔ ላይ የገለጠው እግዚአብሔር ይመስገን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የልጅነት ስልጣን እንዲያው ተሰጥቶኛል
ስሙ በግንባሬ ማኅተም ሆኖኛል
አምላክሽ ወዴት ነው አትበለኝ ጠላቴ
አይቆይም ይመጣል ፈጥኖ ረዳቴ
አዝማች · Chorus
በተከበበች ከተማ የሚያስደንቀውን ምህረቱን
በእኔ ላይ የገለጠው እግዚአብሔር ይመስገን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ