ኦሆሆ በምድር ላይ ኦሆሆ በሰማይ
Ohoho Bemeder Lay Ohoho Besemay
2011 · ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኦሆሆ በምድር ላይ ኦሆሆ በሰማይ
እልልታ በምድር ላይ እልልታ በሰማይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከበረ በዓለም ላይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነገሠ በዓለም ላይ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የወንጌሉ ስራ ድንቅን አደረገ
ጸድቅን እየዘራ ፍርድን አስወገደ
ሽባው ተተርትሮ እውሩ ዐይኑ በራ
ምስኪኑ ከወድቀት ተነስቶ እግሩ ጸና
አዝማች · Chorus
ኦሆሆ በምድር ላይ ኦሆሆ በሰማይ
እልልታ በምድር ላይ እልልታ በሰማይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከበረ በዓለም ላይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነገሠ በዓለም ላይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለነገድ ለቋንቋ ተነገረ አዋጁ
ፍቅርን እንደሰጠን እግዚአብሔር በልጁ
የምስራቹ ቃል ሆነልን ብርሃን
በጨለማ ያሉ አዩት ጌታችንን
አዝማች · Chorus
ኦሆሆ በምድር ላይ ኦሆሆ በሰማይ
እልልታ በምድር ላይ እልልታ በሰማይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከበረ በዓለም ላይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነገሠ በዓለም ላይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቃሉ እየነጐደ ምድርን አለበሰ
የዲያቢሎስን ክንድ እያፈራረሰ
ለኃጢአት እስረኞች ክብደት ጸናባቸው
ኢየሱስ ዋስ ሆነና ነፃ ለቀቃቸው
አዝማች · Chorus
ኦሆሆ በምድር ላይ ኦሆሆ በሰማይ
እልልታ በምድር ላይ እልልታ በሰማይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከበረ በዓለም ላይ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነገሠ በዓለም ላይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ