Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዝናህ የገነነው

Zenah Yegenenew

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በአንተ ደስ ይለኛል የእኔ ጌታ

ልጽና በመንፈስህ እንዳልረታ

አርቄ እያየሁ የጽድቅ አክሊልን

በተስፋ እንድጓዝ እርዳኝ ልጅህን

የርስቴ መያዣ መንፈስህን

ያጽናናኝ ሁልጊዜ እንዳልረሳህ (፪x)

የማትሰለቸኝ የማትረሳኝ

ረዳት ለጉዞዬ ለነፍሴ አጽናኝ

ዓይኔን እንዳላነሳው ከመስቀልህ

ሃሳቤን ጠቅልለው ወደ ሞትህ (፫x)

ዝናህ የገነነው በዓለም ላይ

መቼ ትመጣለህ ፊትህን እንዳይ

በጣም ጓጉቻለሁ የእኔ ጌታ

ኢየሱሴ እንዳይህ ማራናታ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ