የጽዮን ግርማዋ
Yetsiyon Germawa
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የጽዮን ግርማዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
በአባቱ ቀኝ ያለው በላይ ያለው
የንጋቱ ኮከብ ደግሞም የሚባለው
እኛ የምናመልከው ጌታችን እርሱ ታላቅ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ምድር መረገጫው ሰማይም ዙፋኑ
የጽዮን ሙሽራ ግሩም ነው ብርሃኑ
ወጀብ ነጐድጓድም ለርሱ ይታዘዛል
ስሙ ግሩም መንፈስ ነው ሰላምን ይሰጣል
አዝማች · Chorus
የጽዮን ግርማዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
በአባቱ ቀኝ ያለው በላይ ያለው
የንጋቱ ኮከብ ደግሞም የሚባለው
እኛ የምናመልከው ጌታችን እርሱ ታላቅ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም እሩህሩህ ነው
ከአንበሳ መንጋጋ ከእሳት ያወጣ ነው
ልጆቹን ይወዳል እህል ይሰጣቸዋል
ቃሉም ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ይኖራል
አዝማች · Chorus
የጽዮን ግርማዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
በአባቱ ቀኝ ያለው በላይ ያለው
የንጋቱ ኮከብ ደግሞም የሚባለው
እኛ የምናመልከው ጌታችን እርሱ ታላቅ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
አልፋ ኦሜጋ ነው ዘመን አይሽረውም
ሰማይ ምድር ሲያልፉ እርሱ አይለወጥም
ስሙም ለዘለዓለም ታምርን ይሰራል
ደሙ ፍጹም ኃይል ነው ሕይወትን ይሰጣል
አዝማች · Chorus
የጽዮን ግርማዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
በአባቱ ቀኝ ያለው በላይ ያለው
የንጋቱ ኮከብ ደግሞም የሚባለው
እኛ የምናመልከው ጌታችን እርሱ ታላቅ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ