Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምድርና ሞላዋ

Mederna Molawa

2011 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር እሩህሩህና መሃሪ ነው

ከቁጣ የራቀ ምህረቱ ብዙ ነው

እግዚአብሔር ለሚታገሱት ሁሉ ቸር ነው

ምህረቱም በስራው ሁሉ ላይ ነው

ምድርና ሞላዋን በኃይሉ ለገዛው

ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ላለው

ለርሱ እቀኛለሁ አዜማለሁ (፪x)

ስለ ነገሠ ክብር ይገባዋል

ከፍ ከፍ ስላለ ክብር ይገባዋል

ግርማው ስለሚያስፈራ ክብር ይገባዋል

ሥሙ ታላቅ ስለሆነ ክብር ይገባዋል

ምድርና ሞላዋን በኃይሉ ለገዛው

ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ላለው

ለርሱ እቀኛለሁ አዜማለሁ (፪x)

ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካሉ

አፍም ሁሉ ለእርሱ ምሥጋና ያቀርባሉ

መላእክት በሰማይ ለክብሩ ያዜማሉ

ቅዱሳን በናፍቆት በምድር ይቀኛሉ

ምድርና ሞላዋን በኃይሉ ለገዛው

ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ላለው

ለርሱ እቀኛለሁ አዜማለሁ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ