የእኔ ነገ ለእኔስ ብርሃን ነው
Yenie Nege Lenies Berhan New
2011 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለዚህ እላችኋለሁ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና
በምትጠጡት ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት
አትጨነቁ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ አይዘሩም አያጭዱም
በጐተራም አይከቱም የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል
እናንተም ከእነርሱም እጅግ አትበልጡምን? ከእናንተ ተጨንቆ
ከቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማነው?
ስለልብስስ ስለምን ትጨነቃላቹህ? የሜዳ አበቦች እንዴት
እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ አይደክሙም ፤
አይፈትሉምም ነገር ግን እላችኋለሁ ሰለሞንስ እንኳን
በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን
የሜዳን ሳር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ ፣ እናንተ እምነት
የጐደላችሁ እናንተንማ ይልቁን "እንዴት እንግዲህ
ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?" ብላችሁ
አትጨነቁ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ ይህ ሁሉ
እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና ነገር ግን
አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ፣ ጽድቁንም ፈልጉ
ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ነገ ለራሱ ይጨነቃልና
ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል ነገ ለራሱ
ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ [1]
አዝማች · Chorus
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እፈራለሁ
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እጨነቃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ነገ ለሚሆነው ብጨነቅ ባዝን
ትርፉ ማጉረምረም ነው ጌታንም ማሳዘን
ጨንቀቴን ሁሉ ለጌታ ማስረከብ ነው
ስለእኔ ያስባል እርሱ አባቴ ነው
የእኔ ነገ ሙሉ ፀሐይ ነው
የሚያዝበትም ጌታ ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እፈራለሁ
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እጨነቃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የነገ ውለቴ በጌታ እጅ ነው
ጊዜና ሁኔታ በእርሱ ቁጥጥር ነው
የሰማዩ አባቴ በነገው አልፎበታል
ደመናው ይጠፋል ሃዘን ደስታ ይሆናል
የእኔ ነገ ተስፋ ያለው ነው
ተቆጣጣሪው ጌታ እግዚአብሔር ነው
አዝማች · Chorus
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እፈራለሁ
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እጨነቃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ፈተናም ችግር መከራም ቢሆን
ያለአባቴ ፈቃድ አንዳችም ላይሆን
ፈቃዱም ከሆነ ክፉ ለበጐ ነው
የኔም ነገ ሁልጊዜም ብርሃን ነው
የእኔ ነገ ብሩህ ፀሐይ ነው
የሚያዝበትም ጌታ ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እፈራለሁ
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እጨነቃለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሞት እንኳን ቢሆን ለእኔ ጥቅም ነው
ከጌታ ጋር መሆን እጅግ የሚሻል ነው
ጨለማ ይጠብቀኝ ተስፋዬ ብሩህ ነው
የፍጻሜው እድሌ የኔስ ትንሳኤ ነው
የእኔ ነገ ፍፁም ብርሃን ነው
ይሁን ያለውም ጌታ እግዚአብሔር ነው
አዝማች · Chorus
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እፈራለሁ
የእኔ ነገ ለኔስ ብርሃን ነው ለምን እጨነቃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ