Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጉባኤውን ሁሉ ባርከው

Gubaewen Hulu Barkew

2011 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጉባኤውን ሁሉ ባርከው ጌታ

ቃልህን ላክ ፈውስ ይሁንልን

በታላቅ መጐብኘትህ አስበን

የኋለኛውን ዝናብህን ላክልን

እሳት እሳት ያንን የመንፈስ ቅዱስ እሳት (፪x)

ጉባኤውን ተመልከተው ጌታ

የደከመውን ሁሉ አንሳ

የላሉትንም ጉልበቶቼን ሁሉ

ለአምላካቸው ሁሉ አበርታ

ልጆቼ አይዟችሁ በለን ጌታ (፪x)

የታመሙትንም ሁሉ ፈውስ

በታላቅ ምህረትህ አስበን

የታሰሩትንም ሁሉ ፍታ

ጐብኘን የሠራዊት ጌታ

ተነስ ተነስ የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ (፪x)

ታላቁ ስምህ ይባረክ ጌታ

ምህረትህ ብዙ ነው ጠዋት ማታ

ማዳንህ ታላቅ ነው መድኃኒቴ

ክብርህ ይስፋ ጌታ ኢየሱሴ

ለዘለዓለም ክበር ሃሌሉያ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ