Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብቻ ልቤን

Becha Lebien

2020 · ትራክ 7 · 4:56 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንደበት ይታክታል

የሆድን ሁሉ ቢናገር

ለመጣው ለሄደው ሁሉ

የሚያልፍበትን ቢዘረዝር

የሰሚም- የሰሚም ጆሮ ይዝላል

ለጊዜው ለሰሞንም ቢያዝን

ብቻ ልቤን ደግፈው

አልፈዋለው ብርቱውን ቀን

ብቻ ልቤን ደግፈው

አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን

እጠራሃለሁ

በስምህ ውስጥ ሰላም አለ

እጠራሃለሁ

በስምህ ውስጥ ብርታት አለ

በስምህ ውስጥ

እግዚአብሔር

በሥምህ ውስጥ ሰላም አለ

በሥምህ ውስጥ እረፍት አለ

በሥምህ ውስጥ ጽናት አለ

በሥምህ ውስጥ

ከፀሓይ በታች መልስ ባጣሁለት ጉዳይ

ቢያይልም ግርታዬ አይኔን ተክያልህ ሰማይ

ከያዘኝ ከከበበኝ በላም አንተን አምንሃለሁ

ብቻ ልቤን ደግፈው

አልፈዋለው ብርቱውን ቀን

ብቻ ልቤን ደግፈው

አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን

ልቤ ተጠብቆ በሚሆነው ነገር

እታገስሃለሁ አለህ አንድ ነገር

ብቻ ልቤን ጠብቀው

አልፈዋለው ብርቱውን ቀን

ብቻ ልቤን ደግፈው

አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን

በሥምህ ውስጥ ሰላም አለ

በሥምህ ውስጥ እረፍት አለ

በሥምህ ውስጥ ጽናት አለ

በሥምህ ውስጥ

ልብ ብቻውን ሲቀር በሃሳብ ሲወረር

በሁነኛ ነፋስ በማዕበል ሲሰወር

ደጋፊ ከሌለው ማን ከማን ያስጣል

ልብ የወደቀ ቀን ለሞት እጅ ያሰጣል

ልቤን የሚታደግ ብርቱ ግንብ አለቴ

አጥር ሃይሌ ስምህ ነው የተስፋ ጽናቴ

አንተ ነህ እግዚአብሔር ጽኑ መታመኛ

አደራ የምለው አንተን ነው የልቤን መገኛ

በሥምህ ውስጥ ሰላም አለ

በሥምህ ውስጥ እረፍት አለ

በሥምህ ውስጥ ጽናት አለ

በሥምህ ውስጥ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ