ግታው ሰበቤን
Getaw Sebebien
2020 · ትራክ 9 · 4:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከነገር ጅማሬ ፍጻሜ ይልቃል
ቀን ሳለ ጎበዝ ከየት እንደወደቀ ያስባል
የጅማሬው ውበት የዳነበቱ
ደብዝዞ ሳያልቅ በመንገድ ከንቱ
በጸጋ ሽፋን ፋኖ ተማምኖ
ስቆ ለውሃ ብዙ አለና የቀረ ባክኖ
አልፈልገውም ለብታዬን እግሮቼን አድስ
እኔ አልሻም መባከን በልማድ መደንዘዝ
ግታው ሰበቤን ያደከመኝን
ሰበብ በኩሬን የሚያስንቀኝን፤
ግታው ምክኒያቴን የተጫነኝን
ምክኒያት በኩሬን የሚያስጥለኝን
አዝማች · Chorus
መሀል ሰፋሪ እዚም እዚያም
ሁሉ አይቅርብኝ አገም ጠቀም
የለብታ ወንዝ ከባድ ፈተና
ወይ ያልበረደው ወይ እሳት ያልገባው ገና
አቋም በሌለው ከከልካይ ማዶ
በነጻ ክልል ይነጉዳል ፈቅዶ
ግታው ሰበቤን ያለዘበኝን
አክብጄ እንዳልይዝ ያጠመደኝን፤
ግታው ምክኒያቴን የታገለኝን
ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን
ቁጥር 2 · Verse 2
ነግቶለት ህይወት ጉዞ ጀምሮ
ባንተው ምህረት በስንት ተምሮ
ከመንከራተት ተርፎ ያልተረፈ
ዛሬም የሚባክን ልቡ ያላረፈ
ገና
አዝማች · Chorus
ዳግም ባርነት ዳግም እስራት
ባልሰከነች ነፍስ ልጓም በሌላት
ይብቃኝ ምክኒያቴ የተጫነኝ
አጥብቄ እንዳልይዝ ያታገለኝ
ግታው ምክኒያቴን ያደከመኝን
ትጥቄን ያላላ ያለዘበኝን
በመንፈስህ አንቃኝ አዚሜን ገፈህ
የታገትኩበትን ገመዴን ፈተህ
ግታው ሰበቤን ያበረደኝን
ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ