ፍለጋ
Felega
2020 · ትራክ 14 · 4:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሊያገለግልህ የጠራኸው በህዝብህ ፊት የሾምከው
ስንቱ ርቆህ ያገለግላል ለዝናው ክብሩ አድሮ ይዉላል
ስንቱ ርቆህ የራሱን ክብር ያገለግላል
ለዝናው ስሙ ታግሎ ይኖራል
ያላንተ ጉዞ ስም ዝናን ብቻ ይዞ
የስጋ ጥረት በሌለህበት
ያላንተ ክብር በእኔነት ፍቅር
በፀጋ ካባ ለራስ ወከባ
ለከንቱ መንገድ ባንተ ሲነገድ
አዝማች · Chorus
ፍለጋ ክብርን
ፍለጋ ዝናን
ፍለጋ ብልጫን ፍለጋ
ፍለጋ ንዋይን
ፍለጋ ትኩረትን
ፍለጋ ፍለጋ
አምልኮተ ዝና አምልኮተ እኔ
በአምልኮ መልክ ሽፋን በፍቅሬ ተይዤ
በንጉስ ዙፋን ላይ በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ
በውድድር መንፈስ ምስባክ ለታይታ
በትወና ህይወት የኔን ለኔ ዋይታ
ፍለጋ ክብርን
ፍለጋ ዝናን
ፍለጋ ብልጫን ፍለጋ
ፍለጋ ንዋይን
ፍለጋ ትኩረትን ፍለጋ ፍለጋ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሌለህበት ሳውልህ ለዝና ስሜ ስፈልግህ
ተላላ የልቤን ባያገኘው ካንተ ማን ሊሰውረው
ከባዶ ጩኸት ከሌለህበት ዝምታዬ ካገነነህ
ባለህበት ክብሬ ያ ነው ያከበረህ እኔነቴን የሰበረ
ፍለጋዬ ይሁን ለጉዳይህ
ፍለጋዬ ይሁን ለሀሳብህ
ፍለጋዬ ፍለጋዬ ይሁን ለክብርህ
ስራዬን ትመዝናለህ ከመንበርህ ታዬኛለህ
ፍለጋዬን አጥራው መንገዴን ላረካ የቆምኩለትን የራስ ጥሜን
መከሩ ብዙ ነው ስራ አለ በቤቱ
ወደሞት ሚነዳ አለ በየዕለቱ
በራስ ፍቅር ታምሜ መሽቶብኝ ይነጋል
ኢየሱስን ሳያይ ስንቱን ሞት ይቀድማል
አዝማች · Chorus
እድሜያችን ቢበዛ ሰባ ነው ቢያልፍ እንኳን ሰማኒያ
ምን አለን ክብር ምን አለን ንዋይ
ኢየሱስ ካንተ ወዲያ
ምን አለን ዝና ምን አለን ክብር ኢየሱስ ከአንተ ወዲያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ