Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሽኩር

Shekur

2020 · ትራክ 16 · 4:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በእንባ እንዳልዘራሁ

በለቅሶ እንዳልወጣሁ

በሃዘን እንዳላለፍኩ

ነዶዬን ይዤ ተመለስኩ

መልካምነትህን አየው

ጻድቅነትህን አየሁ

በእንባ እንዳልነበርኩ

ነዶዬን ይዤ ተመለስኩ

ይኸው ምስጋናዬን እንካ

ይኸው አምልኮዬን እንካ

ይኸው ዝማሬዬን እንካ

ይኸው እልልታዬን እንካ

ባንተ አይደለም ወይ (፰x)

ስደክም ያኔ ዝዬ

ስበረታም ደግሞ ደግሜ

ቁልቁለት ዳገቱ ሲያዝለኝ

ሽቅብ መውጣቱ ሲከብደኝ

የማያልፍ ሚመስልን ያን ዳገት

አልፌው ስገኝ ድንገት

አልረሳም ያን ቀውጢ ጊዜ

ሲርቀኝ ሃዘን ትካዜ

ይኸው ምስጋናዬን እንካ

ይኸው አምልኮዬን እንካ

ይኸው ዝማሬዬን እንካ

ይኸው እልልታዬን እንካ

ባንተ አይደለም ወይ (፰x)

ማን አለው ብሎኛል ስደክም

የተማመንኩበት ሲከስም

የያዘኝ ጸጋህ በብርቱ

በማልፍበት አልፎ የረዳኝ በሌቱ

የብቸኝነቴ አምላክ

የጓዳዬ የሚስጥሬ ጌታ

ሰማህ ጩኸቴን ሰማህ

ሰማህ እንባዬን ሰማህ

ይኸው ምስጋናዬን እንካ

ይኸው አምልኮዬን እንካ

ይኸው ዝማሬዬን እንካ

ይኸው እልልታዬን እንካ

ባንተ አይደለም ወይ (፰x)

ሽኩር ጉዌታ ሽኩር - ሽኩር (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ