በሩን ክፈቱ
Berun Kefetu
2020 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሥም ሁሉ በላይ ኃያል ሥም አለው
በዚህ ሥም አምነን ድነናል ይኸው
ምስክሮቹ ነን ሕይወት ደርሶናል
ሰማይ ሲጎበኘን ለዓለም በርተናል
ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ሥም
ከነበርንበት ዓለም የለንም
የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ክብር
ሰውን ኑ እንላለን አልፈን ከምድር
አዝማች · Chorus
አምላክ ሥጋ ሆነ ለእኛ ማለደ
ከአብ አስታረቀን ስርየት ወረደ
ሕያው ልጆቹ ነን ዳግም ወልዶናል
ዘላለም ሲያገኘን ከሞት ጠፍተናል
ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ሥም
ከነበርንበት ዓለም የለንም
የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ክብር
ሰውን ኑ እንላለን አልፈን ከምድር
ቁጥር 2 · Verse 2
እናንት መኳንንቶች በሩን ክፈቱ
የክብር ንጉሥ ይግባ በሩን ክፈቱ
ይሄ ንጉሥ ማነው እርሱ እግዚአብሔር ነው
የክብር ሁሉ ጌታ እርሱ እግዚአብሔር ነው
እርሱ እግዚአብሔር ነው (፪x)
እርሱ እግዚአብሔር
የክብር ሁሉ ጌታ የክብር ሁሉ ገዢ
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል (፪x)
የሰማይ የምድሩ የልዑላን ጌታ
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል (፪x)
አዝማች · Chorus
ሆሆ ኃያሉ እግዚአብሔር
እርሱ እኛን ጎበኘ
እንድንዘምርለት ዙሪያው ሰበሰበን
ሆሆ እግዚአብሔር ረዳን
እግዚአብሔር አሰበን
በየደረስንበት ኃያል መዝሙር ሆነን
ምሥጋና የተገባው እርሱ ነው
ውዳሴ የተገባው እርሱ ነው
ለእኛ ታየን መድኃኔዓለም
እንደርሱ የለም ዘላለም
ለእኛ ተገለጠ መድኃኔዓለም
እንደርሱ የለም ዘላለም
ዝማሬ የተገባው እርሱ ነው
ስግደትም የተገባው እርሱ ነው
ለእኛ ታየን መድኃኔዓለም
እንደርሱ የለም ዘላለም
ለእኛ ተገለጠ መድኃኒዓለም
እንደሱ የለም ዘላለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ