እረኛ
Eregna
2020 · ትራክ 6 · 4:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖረ
ልቡ ስለመንጋው ያደረ
ለአንዲት ምስኪን ነፍስ ግድ እያለው
ብዙ አሉኝ ብሎ አንዷን የማይተው
ይሄዳል ያለእረፍት ሁሉ ጋ
የጠፋችውን ያቺኑ ፍለጋ
ሲያገኛት ሌላ እንደሌለው
ደስታው መለኪያም የለው
የባዘነውን የሚመልስ
የጠፋውን የሚፈልግ
የተሰበረውን የሚጠግን
የሚያጸና የደከመውን
አዝማች · Chorus
ይህ ነው የእኔ እረኛ
ይህ ነው የእኔ መዳኛ
ይህ ነው የእኔ መጽናኛ
ኢየሱስ መልካሙ እረኛ
መታመኛዬ መጠገኛዬ
መደገፊያዬ መታደጊያዬ
ጠያቂ አለኝ ጠያቂ
ፈላጊ አለኝ ፈላጊ
ጠያቂ አለኝ ጠያቂ
መሽቶም ሲነጋ ጠባቂ
ይህ ነው የእኔ መጽናኛ
ኢየሱስ መልካሙ እረኛ
ቁጥር 2 · Verse 2
ውዴ የሚታደገኝ ራሱን ሰጥቶ
የሚያውቀኝ ከልብ በስም ለይቶ
ለአፍታም ለቅጽበት አይለየኝ
ለሚሰማሩብኝ አይተወኝ
የእረኞች አለቃ እረኛዬ
የገዛኝ በፍቅር መጋቢዬ
ኢየሱስ የነፍሴ አባት ጠባቂዋ
ከዱር ከገደሉ ማምለጫዋ
የባዘነውን የሚመልስ
የጠፋውን የሚፈልግ
የተሰበረውን የሚጠግን
የሚያጸና የደከመውን
አዝማች · Chorus
ይህ ነው የእኔ እረኛ
ይህ ነው የእኔ መዳኛ
ይህ ነው የእኔ መጽናኛ
ኢየሱስ መልካሙ እረኛ
መታመኛዬ መጠገኛዬ
መደገፊያዬ መታደጊያዬ
ጠያቂ አለኝ ጠያቂ
ፈላጊ አለኝ ፈላጊ
ጠያቂ አለኝ ጠያቂ
መሽቶም ሲነጋ ጠባቂ
ይህ ነው የእኔ መጽናኛ
ኢየሱስ መልካሙ እረኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ