ሩጫው
Ruchaw
2020 · ትራክ 5 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሩጫው አይደል ወይ ሰላምን ፍለጋ
እርካታን ፍለጋ
ሁሉም በየፊናው ሚለው ደፋቀና
ሚለው ጎንበስ ቀና
ገንዘብ ቁስን እንጂ እረፍት መች ይገዛል
በየደረሰበት ሰው ሃሳብ ይገዛል
ጭንቀት ይሸምታል
አዝማች · Chorus
እረፍት መገኛው ኢየሱስ
ሰላም ማደሪያው ኢየሱስ
ደስታ ሀገሩ ኢየሱስ
ቁጥር 2 · Verse 2
እረፍት መኖሪያው ኢየሱስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሀብት ጥሪት ይዞ የተትረፈረፈ
ከእድሜ ልክ ያለፈ
ሰላም ከሌለበት ሰላምን ፍለጋ ስንቱ ነው የዋለ
የተንከራተተ
ዛሬን እረፍት አጥቶ ለነገ ያልማል
ነገም ነገን ሲቀርጽ ሳያልቅ ዘመን ያልቃል
አዝማች · Chorus
እረፍት መገኛው ኢየሱስ
ሰላም ማደሪያው ኢየሱስ
ደስታ ሀገሩ ኢየሱስ
ቁጥር 4 · Verse 4
እርካታው መኖሪያው ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ቁጥር 5 · Verse 5
በላው ጠጣው ትርፌ ምንድነው?
አጌጥኩ ለበስኩ ትርፌ ምንድነው?
ተማርኩ አወኩ ትርፌ ምንድነው?
ምድር ሞላልኝ ትርፌ ምንድነው?
ኸረ እኔ በእንጀራ ብቻ ኸረ አልኖርም
ኸረ እኔ በምድሩ ብቻ ኸረ አልኖርም
ክፍተቴ ሌላ ነው ጉድለቴ
የማልሞላው በማንነቴ
እሮጬ እሮጬ ትርፌ የእኔ ድካም ነው
የነፍስ እርካታዬ ጌታ በአንተኮ ነው
እንኳን ያንተ ሆንኩኝ አወኩህ እንኳን
እንዳልችል ሆኛለሁ ለሌላ እንዳልሆን
የማምነው እውነት በፍቅር ይዞኛል
ሌላ ሌላ እንዳላይ ውስጤን ሞልተኸዋል
አሰብኩት እራሴን ከአንተ ውጪ
አሰብኩት ወጥቼም ከቤትህ
ባዶ ነኝ ቅብዝብዝ የሌለኝ እረፍት
እኔ አልችልም ሰው አልሆንም በሌለህበት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ