ሁሉን በስርህ
Hulun Besereh
2020 · 6:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፊደል ተግጣጥሞ የቱ ቃል ገለጠህ
ቃላት ተሰካክተው ምን ቢባል ተረከህ
ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚዓብሔር ብቻ
እራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ
የተባልከው ሁሉ ካንተ በታች ሆኗል
ለፍጥረት ሚበዛው ላንተ አቅም አንሶታል
ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚዓብሔር ብቻ
እራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ
መጀመርያም መጨረሻም የሌለህ
አልፋ ኦሜጋ ፊተኛም ኋለኛም የሌለህ
አዝማች · Chorus
እግዚዓብሔር አንተ ነህ (፪x)
የእኔ ትልቅ አንተ ነህ
የእኔ ጀግና አንተ ነህ
ሁሉን በስርህ አስተዳዳሪ
በላይ ለሁሉ ሁሉን ፈጣሪ
የግዙፍ ግዙፍ የትልቅ ትልቅ
ቃል በማይደፍረው የከፍታ ጥግ
አንተ እግዚዓብሔር አንተ ብቻ ነህ
ትልቅ መሳዩን ትንሽ ያደረግህ
ጀግና መሳዩን ያንበረከክህ
ጠቢብ መሳዩን ሞኝ ያደረግህ
ያለው መሳዩን ባዶ ያደረግህ
የለም ያሉህ የሉም
ዛሬም የሚሉህ ነገ አይኖሩም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይገርመኛል ትጋታቸው የከንቱነት ጥበባቸው
ከአንተ ውጪ ሕይወት ማሰባቸው
አንተው ባበጀኸው አእምሮ
ባንተ ጥበብ ተቀምሮ
እስትንፋስ ለግሰህ በእፍታህ
ባምሳልህ ሰርተኸው ስታበቃ
የለህም የሚልህ ማን ነው
እኮ የለህም የሚልህ ማን ነው
ለመኖርህ የእርሱም መኖር ምስክር ነው (፫x)
አዝማች · Chorus
ለመኖርህ የእኔም መኖር ምስክር ነው
ሉዓላዊነት ከጥንት ከዓለማት በፊት የነበረ
አለህ የለህም ቢባል ከመኖር ያልተገደበ
እግዚዓብሔር አለህ በማደርያህ
እግዚዓብሔር አለህ በዙፋንህ
አለህ በማደርያህ
አለህ በዙፋንህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ