Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተናገር

Tenager

2020 · ትራክ 15 · 6:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባነበብን ቁጥር ባወቅነው የማንለምደው ቃልህን

በገባን ቁጥር ባወቅነው ምንፈልገው ቃልህን ነው

ዛሬም እንድትልልን ሳይሆን ልትል ያሰብከው ያግኘን

ያለመከልከል ተናግረህ ያለገደብ ስራብን

መንፈስህ ይግዛን ይስፈንብን በሙላት

የልብህ ሀሳብ ያጥምደን የሚያቆመን ያ ነው በጽናት

እናድጋለን እንጂ ሰርክ ወዳንተ

ልናድግ አይቻለንም ባንተ ላይ

ከፍለን ባወቅንህ ቁጥር

ዝቅ እንበል እንይ ወደላይ

ምን ብናውቅ ጥበብ ቢጠጋን

ሲመስለን ያወቅን የበቃን

አናውቅም ባወቅን ቁጥር

ደቀ መዝሙር ነን ሁሌ ባንተ ስር

ተማሪዎች ነን ሁሌ ልጆችህ

መቼም በማንጨርሰው ትምህርትህ

ከፍለን ባወቅን ጥቂት

ትሁት አድርገን ባንተ ፊት

ታማኝ አድርገን ለቃልህ

አቅናን ለውድ ሀሳብህ

መስታወት በሆነው ቃልህ

አብቃን ለልብ መንገድህ

ተናገር ኢየሱስ

ተናገር በሀይል እንሰማሀለን

ተናገር መንፈስቅዱስ

ተናገር በሙላት እንሰማሀለን

ተናገር እንሰማሀለን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ