Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ረግቻለው

Regechalew

2020 · ትራክ 11 · 5:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለሰላሜ ሚሆነኝን አውቂያለሁ አግኝቻለሁ

ለእፎይታዬ ሚበጀኝን አምኛለሁ ተቀብያለሁ

የእግዚአብሄር ልጅ በርቶልኛል በመንፈሱ ረግቻለሁ

ላልወሰድ በምድር ተረት ለዘላለም ታትሜያለሁ

ከአለም ዋኖች በተሰወረ

ከጠቢባን ዘንድ ባልነበረ

የሞኝነት በሚመስል ታምር

እኔ አርፍያለሁ ባንተ ማመን ሚስጥር

ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል

ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

ሰላም ረግቶልኛል ፍቅርህ ዘልቆልኛል

ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

የማይነጥፍ ነው ሰላሜ የማያርፍ ነው እረፍቴ

ማደርያህ ልሆንህ ፈቅደህ ገብተሃልና ከህይወቴ

የማይደበዝዝ ፍቅርህ ነው ሽንገላም ወረትም በሌለው

ካንተ ያልተቀበልኩት ምን አለኝ ቀረ ምለው??

አንተ ሞልተኽኛል ህይወት በዝቶልኛል

ረክቻለሁ ልጅህ ተብያለሁ

ባንተ ደስ ይለኛል ሰላም ረግቶልኛል

ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

በሰማያዊው በረከት በራስህ ተባርክያለሁ

እዚህ እንዳልናወጥ ከእቅፍህ ገብቻለሁ

አልሸበርም በአለም በሚሰማው ክፉ ወሬ

ባለኸኝ ረግቼ አለሁ በያዝከኝ እስከዛሬ

ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል

ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

ሰላም ረግቶልኛል ፍቅርህ ዘልቆልኛል

ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

አንተን ይዞ ያልረካ ማነው

አንተን ይዞ ያልሰከነ ማነው

አንተን ይዞ የባከነ ማነው

አንተን ይዞ የባዘነ ማነው

እኔ ረክቻለሁ

ሰላም አግኝቻለሁ

ረግቻለሁ አመሰግናለሁ

ሰላም በዝቶልኛል

ጸጋህ ሸፍኖኛል

አይቼሃለሁ አመሰግናለሁ

ለበዛልኝ ሰላም ለበዛልኝ ፍቅርህ

ለበዛልኝ ህይወት ለበዛ ምህረትህ

ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ሞገስ

ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ሞገስ

ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ሞገስ

ይብዛልህ ክብር እየሱስ ይብዛልህ ሞገስ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ