በጐነቴ
Begonetie
2014 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም ከአንተ በቀር
ከአንተ በቀር መመኪያም የለኝም ከአንተ በቀር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተስፋ ማደርገው አለኝ የምለው
በሕይወት ዘመኔ አንተኑ ብቻ ነው (፪x)
አንተኑ ብቻ ነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓሣ ከውኃ ውስጥ ሲወጣ
ከቶ እንደሌለው የመኖር ተስፋ
እኔም ያለአንተ መኖር አልችልም
ነፍሴ/ልቤ ወደደህ አልለይህም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በጐነቴ (፬x) አለቴ መድሃኒቴ
እወድሃለሁ ጉልበቴ
እወድሃለሁ ጉልበቴ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ስገረምና ስደነቅ ሁሌ
በአንተ ቤት ይለቅ ጌታ ዘመኔ
ደግ እንዳንተማ አይቼ አላውቅም
ሁሌ መልካም ነህ አትለወጥም (፪x)
አዝማች · Chorus
ተስፋ ማደርገው አለኝ የምለው
በሕይወት ዘመኔ አንተኑ ብቻ ነው (፪x)
አንተኑ ብቻ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ