ፊትህን ሳይ
Fitehen Say
2014 · ትራክ 8 · 5:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፊትህን ሳይ እጠግባለሁ
ፊትህን ሳይ እጽናናለሁ እኔ እጽናናለሁ
ፊትህን ሳይ እበረታለሁ
ወደአንተ መጥቼ ሁሉነረሳለሁ
እምባዬ ታብሶ ደስታን እሞላለሁ (፪x)
እራሴን ሳየው ማንነቴን ሳውቀው
የደስታዬ ምንጭ ምንም የለም ከአንተ ውጭ
አዝኜ መጥቼ ስቄ እመለሳለሁ
ቀና ብዬ ሳይህ ፊትህ ጠጋ እላለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
የመጽናኛዬ ቦታው የለቅሶ ሃዘኔ መርሻው
ፊትህ ነው (፫x) ደስ የሚያሰኘው
ፊትህ ነው (፫x) ደስ የሚያሰኘው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሌላ እኔ አልሻም የልብ የሚሆን የለም
ሁሉም አላፊ የዚህ ዓለም ክብር ጠፊ
ፊቴን መልሻለሁ አይጠቅመኝም ሌላ
አንተኑን መመልከት ያዋጣኛልና (፪x)
አዝማች · Chorus
የመጽናኛዬ ቦታው የለቅሶ ሃዘኔ መርሻው
ፊትህ ነው (፫x) ደስ የሚያሰኘው
ፊትህ ነው (፫x) ደስ የሚያሰኘው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ