ዘመኔን የሰጠሁት
Zemenien Yesetehut
2014 · ትራክ 5 · 4:20 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘመኔን የሰጠሁት
ጉብዝናዬን ለእርሱ ያደረኩት
አልጣለኝም አልረሳኝም
ይዞ ሲመራኝ ሲያስመልጠኝ
ሲያሻግረኝ ዛሬን አሳየኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለዚህ ልበል ላውራው ልናገር
የደረሰልኝ እርሱ እግዚአብሔር
የተረሳውን አስታዋሽ እርሱ
ዛሬም እላለሁ የለም እንደእርሱ
ቀየረው ገብቶ በቤቴ
አንገት መድፋት ቀረ በሕይወቴ
ታማኝ ነው የምስኪን ወዳጅ
ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ
ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ
ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ገባ ገባ ገባ ኢየሱስ ቤቴ
አማረ በእርሱ ሕይወቴ
ተለወጠ ያ ማንነቴ
አንድ ሰው ነኝ በመድሃኒቴ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ቀናልኝ መንገዴ የሚያዋጣውን ይዤ
ሁሉ አማረልኝ በዚህ በወዳጄ
ክብርን ሳላስበው መጣ ወደቤቴ
ተደላድያለሁ አርፌ በአባቴ
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
ወዳጄ ቤቴ ሲገባ
አባቴ ቤቴ ሲገባ
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
የጠራኝ ቤቴ ሲገባ
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
ቁጥር 5 · Verse 5
ምናገረው አለኝ ክተደረገልኝ
ቸር ነው የእኔ አባት ዛሬ ላይ አቆመኝ
አንደበቴን ልክፈት ላውራው ልመስክር
ከጌታዬ ሌላ አልውቅም ክብር
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
ወዳጄ ቤቴ ሲገባ
አባቴ ቤቴ ሲገባ
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
የጠራኝ ቤቴ ሲገባ
ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ