Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የተጣለው አለ

Yetetalew Ale

2014 · ትራክ 1 · 5:03 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ግድ ሆነበት በግዞት ማለፍ

ባለ ራዕዪው ሲገፋ ለእውነት

ቀን ጠብቆ ተስፋ ሊፈጸም

ተግዳሮቱ እጅግ ቢበዛም

ቃል ያወጣው ታማኝ ነውና

ሁሉ አልፎ ድል እንደገና

ተሰራጨ መልካሙ ዜና

የተጣለው በሕይወት አለና

አለ (፫x) የተጣለው አለ

አለ (፫x) የተረሳው አለ

የተጣለው አለ

የተረሳው አለ (፬x)

የተጣለው አለ

የተረሳው አለ (፫x)

የተጣለው አለ

አለ አለ (፬x)

አለው ጊዜ አለው

ኧረ አለው ሰዓት አለው (፪x)

ምንም ቢረዝም መንገዱ

ሁሉ ለአንዱ ሰገዱ

ቀን ጠብቆ ሲመጣ

በሹመት ዕጣው ወጣ (፪x)

ለሁሉም ጊዜ አለው ለሁሉም

ለሁሉም ቀን አለው ለሁሉም

ወንድሞቹ ወስደው ቢጥሉትም

ባልፈጸመው ኃጢአት ቢከሰስም

ህልሙ ሳይፈጸም ቃል ያለው አይሞትም (፪x)

ለሁሉም ጊዜ አለው ለሁሉም

ለሁሉም ቀን አለው ለሁሉም

ለሁሉም ጊዜ አለው ለሁሉም

ለሁሉም ቀን አለው ለሁሉም

ወንድሞቹ ወስደው ቢጥሉትም

ባልፈጸመው ኃጢአት ቢከሰስም

ህልሙ ሳይፈጸም ቃል ያለው አይሞትም (፪x)

አይሞትም (፫x) ህልም ያለው አይሞትም

አይሞትም (፫x) ህልም ያለው አይሞትም

ህልም ያለው አይሞትም

ቃል ያለው አይሞትም (፪x)

ቃል ያለው አይሞትም

ህልም ያለው አይሞትም (፪x)

ቃል ያለው አይሞትም

ህልም ያለው አይሞትም

ቃል ያለው አይሞትም

ቃል ያለው አይሞትም

ህልም ያለው አይሞትም

ቃል ያለው አይሞትም

አይሞትም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ