አላለቅስም
Alaleqsem
2014 · ትራክ 7 · 6:04 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዛሬም ለቅሶ ዋይታ ዋይታ
የዚህ ምድር ኑሮ የለውም እርካታ
ጊዜው ሲደርስ ያኔ መምጫው የጌታዬ
ፊት ለፊቴ ሳየው እርሱ ነው ደስታዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
አላለቅስም አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ
የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር
ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘለዓለሜ በዚያ በክብር
በአብ ቀኝ በደስታ ለመኖር
በእርግጥ ናፍቄያለሁ ደርሳለሁ
የታረደውን በግ መሲሁን አያለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አላለቅስም አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ
የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር
ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
በዚህ ምንም የለኝ የለኝ
የሰው ዓይን ያላየው ያላየው
በእጅ ያልተሰራው እርስቴ
እንዴት ያማረ ነው የላይኛው ቤቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
አላለቅስም አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ
የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር
ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የፍጥረት ሩጫ ሲገታ
ለምድሩ በጊዜው ሲያበቃ
ሙሽራው በድንገት ሲመጣ
ፍጻሜን ያገኛል የቅዱሳን ተስፋ (፪x)
አዝማች · Chorus
አላለቅስም አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ
የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር
ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ