Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰው ቢጠየቅ

Sew Biteyeq

2014 · ትራክ 10 · 4:17 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰው ቢተየቅ ስለምኞቱ

አለው ብዙ የሚናገረው

ዛሬ ታይቶ ስለሚጠፋ

ይጨነቃል ነገን ሳያውቀው

የእኔ መሻት አንድ ነገር

ስኖር ሳለሁ በዚች ምድር

ሁልጊዜ እንድኖር ከአንተ ጋር

አምላኬ ሆይ ይብዛልኝ ፀጋህ

ወዳጄ ሆይ ይብዛልኝ ፀጋህ

አባቴ ሆይ ይብዛልኝ ፀጋህ

የእኔ ቦታ ይሁን አንተ ጋር

አድራሻዬ ከዙፋንህ ስር

ዛሬም ፀጋህ ያግዘኝና

አልታጣም ሁሌ ከእግርህ ስር (፪x)

በምድር ያለው

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

ምንም ቢለፋ ምንም ቢደከም ሰው የለም ብርቱ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

በምድር የሚገኝ ፍፁም ያልሆነ ጊዜያዊ ደስታ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

ዕድሜ የሌለው እንደ እንፋሎት ታይቶ የሚጠፋ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ (፪x)

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ (፪x)

አልፈልግም ሌላ ሌላ ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ

አይሆነኝም ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ

አልመኝም ሌላ ሌላ ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ

አያምረኝም ሌላ ሌላ ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ

ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ (፪x)

ዘለዓለሜ ይሁን አንተ ጋር

አድራሻዬ ከዙፋንህ ስር

ዛሬም ፀጋህ ያግዘኝና

አልታጣም ሁሌ ከእግርህ ስር (፪x)

በምድር ያለው

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

ምንም ቢለፋ ምንም ቢደከም ሰው የለም ብርቱ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

በምድር የሚገኝ ፍፁም ያልሆነ ጊዜያዊ ደስታ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ

ዕድሜ የሌለው እንደ እንፋሎት ታይቶ የሚጠፋ

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ (፪x)

ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ