ስለበላሁ
Selebelahu
2014 · ትራክ 12 · 4:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለበላሁ ስለጠጣሁ አልከተልህም እኔ
ፈቃድህን እያደረኩ እኖራለሁ በዘመኔ (፪x)
አይረሳኝ ትላንት ያደረገው
አስገረመኝ ለካ እርሱ ታማኝ ነው
አሰናብቶ ሌላውን ሲሸኝ
ሊሰራብኝ እኔን ግድ/ቆይ አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ
አንተ የሕይወት ቃል አለህ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (፪x)
ጌታ አንተን ብዬ ስምህን ጠርቼ
ነገር የሞላ ቀን ስራህን ሰርቼ
በሆዴ እንዳልታለል ሲሞላ የልቡ ደርሶ
እንዳይሸሽ ጥሎ እንዳይሄድ ባመጣው እግሩ ገስግሶ
አይሆነው ያለአንተ ኑሮ ልቤ አውቆሃል ከአምናው ዘንድሮ
አዝማች · Chorus
እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ
አንተ የሕይወት ቃል አለህ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወስኜ ተነሳሁ ልከተልህ አንተን
ወደ ኋላ ትቼው የራሴን ነገሬን
አንተው ጋር ይሻለኛል ቢሞላም ቢጐድልም ሁሉ
ከደጅህ የትም አልሄድም እቤትህ ሁልጊዜ ሙሉ
ደግ ነህ እጅህ ሰፊ ነው
ዘመኔ ከእግሮችህ ስር ነው
አዝማች · Chorus
እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ
አንተ የሕይወት ቃል አለህ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ