ተጽናና
Tetsnana
2014 · ትራክ 11 · 4:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መከራው በዝቶ ዛሬማ ጭንቅ ሆኖብሃል
ሚያዝ ሚጨበጥ ከፊትህ ሁሉ ርቆሃል
ተስፋ በመቁረጥ በርህን ዘግተህ ተቀምጠህ
አበቃ የእኔማ ነገር ብልህ ደምድመህ
ዜናው ዜናው ተሰማ
የፍቅር አምላክ አለና ወገን ተጽናና
አዝማች · Chorus
የመጽናናት አባት የርህራሄ አምላክ
ከአንተ ጋር ነው
ከአንቺ ጋር ነው
ከእኛ ጋር ነው
ከእኛ ጋር ነው (፪x)
ስለዚህ ወንድሜ ስለዚህ ወገኔ ተጽናና
ኢየሱስ አለና (፬x)
ኢየሱስ አለና (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተደግፈኸው አልጣለህ እርሱን ተማምነህ
ተተግተኸው አልሸሸህ ደካማ ሆነህ
ዓይኖቹ ዛሬም ያያሉ ከቶ አልደከሙም
ሰፊ ትከሻው ብርቱ ነው ይሸከማሉ
አይዞህ አይዞህ ተጽናና
ክብርህን ጥለህ አምልከው ላደረገህ ቀና
አዝማች · Chorus
የመጽናናት አባት የርህራሄ አምላክ
ከአንተ ጋር ነው
ከአንቺ ጋር ነው
ከእኛ ጋር ነው
ከእኛ ጋር ነው (፪x)
ስለዚህ ወንድሜ ስለዚህ ወገኔ ተጽናና
ኢየሱስ አለና (፬x)
ኢየሱስ አለና (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ እያለ የምን ማዘን ነው
ለእርሱ አስረክቦ እርፍ ማለት ነው
ሃዘኔ ጠፍቶ እምባዬ ታብሷል
ሁሉም አለፈ አስረስቶኛል
አላዝንም ከእንግዲህ በቃ እኔ (፬x)
ጌታ እያለ ከጐኔ
እርሱ እያለ ከጐኔ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ