ኑ ደስ ይበለን
Nu Des Yebelen
2014 · ትራክ 3 · 5:18 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አለ እንደገዛ አለ እንደከበረ (፪x)
ፍጥረት ሁሉ ያምልከው
ይገባዋል እርሱ ጌታ ነው
ኑ ደስ ይበለን በእርሱ
ሃሴት እንዳድርግ በንጉሡ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኑ ደስ ኑ ደስ ይበለን
ለእግዚአብሔር እንዘምር (፬x)
ለመድሃኒታችን ዕልል እንበል
በምሥጋና ፊቱ ዘወትር እንቅረብ
በዝማሬ እና በዕልልታ ሆታ
ታላቅ እናድርገው ይህንን ጌታ
ኑ ደስ ይበለን
ለእግዚአብሔር እንዘምር (፬x)
የምድር ጥልቁቆች በእጁ ናቸው
የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው
እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የእርሱ ናት
እጁ የብስን አበጀ እጁ እኔን አበጀ
የበላይነቱን ፍጥረት አወጀ (፪x)
አዝማች · Chorus
አለ እንደገዛ አለ እንደከበረ (፪x)
ፍጥረት ሁሉ ያምልከው
ይገባዋል እርሱ ጌታ ነው
ኑ ደስ ይበለን በእርሱ
ሃሴት እንዳድርግ በንጉሡ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኑ ደስ ይበለን
ለእግዚአብሔር እንዘምር (፬x)
የአህዛብ አማልክት ጣኦታት ናቸው
ሁሉ ነገር ያላቸው ግን የሌላቸው
የፍጥረት ሁሉ ጌታ ሰማይን ሰራ
ክብር ይኸው በፊቱ ሞገስ ይኸው በፊቱ
በመቅደሱ ውስጥ አለ ውበቱ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኑ ደስ ኑ ደስ ይበለን
ቁጥር 4 · Verse 4
ለእግዚአብሔር እንዘምር (፬x)
ለመድሃኒታችን ዕልል እንበል
በምሥጋና ፊቱ ዘወትር እንቅረብ
በዝማሬ እና በዕልልታ ሆታ
ታላቅ እናድርገው ይህንን ጌታ
ኑ ደስ ይበለን
ለእግዚአብሔር እንዘምር (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ