ተወለደ
Tewelede
2014 · ትራክ 13 · 4:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የእግዚአብሔር ፈቃድ በልጁ ሊፈጸም
ራሱን ዝቅ አድርጐ ወረደ ለዓለም
በምድር ሊሰማ ሰላምና ደስታ
ከድንግል ማሪያም ተወለደ ጌታ (፬x)
አዝማች · Chorus
ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች
ዛሬ በዳዊት ከተማ
እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x)
እረኞች ለማየት እጅጉን ጓጉለት
ሰባ ሰገል መተው ወድቀው ሰገዱለት
የፍጥረታት ጌታ የዓለም ሁሉ ንጉሥ
ከአብ ሊያስታርቀን ተወለደ ኢየሱስ (፬x)
አዝማች · Chorus
ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መላዕክት አበሰሩ የምስራቹን ቃል
ዛሬ በቤቴልሄም ወንድ ልጅ ተወልዷል
ምድር ዕልል ትበል ታሰማ ምሥጋና
ሕዝቡን የሚታደግ መሲህ መጥቷልና (፬x)
አዝማች · Chorus
ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች
ዛሬ በዳዊት ከተማ
እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ