Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በወይኑ ሃረግ

Beweynu Hareg

2014 · ትራክ 4 · 4:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በወይኑ ሃረግ ፍሬ ባይገኝ

እንዲሁም በለስ ባታፈራ

እኔ ግን (፪x) በመድሃኒቴ አምላክ

ደስ ይለኛል (፬x)

ማጉረምረም ቢሞላኝ መከራው

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

ልቤን በስብራት ቢያደቀው

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

እምነቴን ቢያናውጥ የሚታየው

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

ውስጤም ሲደነግጥ በሚሰማው

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

እርሱ አለኝና ረዳቴ

ልምንስ ልሥጋ ሆኖኝ ጉልበቴ

በሁኔታዎች አልመዝነውም

ለዘለዓለም ከእኔ ጋራ ነው (፪x)

ጌታ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ከእኔ ጋራ ነው

ጌታ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ተስፋዬ ጨልሞ ባይኖር መላ

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

ያመንኩት ወዳጄ ቢሆን ሌላ

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

ሰማዩ ባይኖረው ምንም ደመና

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

ባዶ ሸለቆው ውኃ ባይሞላ

(እኔ ግን (፪x) ደስ ይለኛል)

እርሱ አለኝና ረዳቴ

ልምንስ ልሥጋ ሆኖኝ ጉልበቴ

በሁኔታዎች አልመዝነውም

ለዘለዓለም ከእኔ ጋራ ነው (፪x)

ጌታ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ከእኔ ጋራ ነው

ጌታ ከእኔ ጋራ ነው

ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ