በጉባኤው መሃል
Begubaiew Mehal
2013 · ትራክ 5 · 4:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በጉባኤው መሃል በአንድ አባት ልጆች ላይ
የተገፋፋ ሰው አንድ ላይ ያመልክሃል
አንድ ላይ ያመልካል
ውስጡን እያመመው ጥላቻው በርትቶ
ወድሃለው ይላል ህዝብህ ቤትህ ገብቶ
አንድ ላይ ተቀምጦ
ስንበላም አንድ ላይ
ስንጠጣም አንድ ላይ
ስንገባም አንድ ላይ
ስንወጣም አንድ ላይ
ይህን ሁሉ ዘምን አንድ ላይ ኖረናል
ውስጥ ውስጡን ተባልተን ግን ተለያይተናል
ምን ያደርጋል
አዝማች · Chorus
ፍቅር አይደለም ዎይ ያገናኘን
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር አይደለም ዎይ ያሰባሰበን
ኢየሱስ አይደለም ዎይ ያገናኘን
ጌታ አይደለም ዎይ ያሰባሰበን
የስስት ጨርቃችን መጨረሻው ብል ነው
ለዛሬ ያልሆነ ፍቅራችን ለመች ነው
ኧረ ለማንስ ነው
ከፍቅሩ ባለቤት ከሆነ ውሎዋችን
በአንድነት ይገለጥ እውነት አምልኳችን
በፍቅር አምልኳችን
ቁጥር 3 · Verse 3
ስንበላም አንድ ላይ
ስንጠጣም አንድ ላይ
ስንገባም አንድ ላይ
ስንወጣም አንድ ላይ
ይህን ሁሉ ዘምን አንድ ላይ ኖረናል
ውስጥ ውስጡን ተባልተን ተለያይተናል
ምን ያደርጋል
አዝማች · Chorus
ፍቅር አይደለም ዎይ ያገናኘን
ቁጥር 4 · Verse 4
ፍቅር አይደለም ዎይ ያሰባሰበን
ኢየሱስ አይደለም ዎይ ያገናኘን
ጌታ አይደለም ዎይ ያሰባሰበን
ቁጥር 5 · Verse 5
እምነት ቢሞላ ዕውቀት ቢከበኝ
ልሳን መናገር ትንቢት ቢኖረኝ
ሥጋዬን ለእሳት ብሰጥ ፈቅጄ
ባልነፍግ ለድሆች ያለኝን ከእጄ [1]
ፍቅር የሌለው እልፍ ደግነት
ጌታ የሌለበት መንፈሳዊነት
ወዴት ወዴት ነው ይህ ከንቱ ጉዞ
በሃሜት ታዝሎ በቂም ተይዞ
ዞሮ ለማን ነው ይህ ጥል ግርግር
አቤል ከቃየል የማይሆን አጥር
ጐራ ለይቶ ይቅር ማድሩ
የእውነት ፍቅር ይግባ መንደሩ
የባላንጣችን ደስታው ይደፍርስ
በፍቅር ዘምተን ሰላም እንመልስ
የቁርሾን ዘመን ይበቃ ብለነው
መዘናጠሉ ነው ወዲያ እንጣለው
ፍቅር ይበቀለው
በረከት ደርሶ ደጅ አይመለስ
የተወሰድው ክብርም ይመለስ
ፍቱን መድሃኒት ፍቅር ነው ፈውሱ
ለምድሪቱ ቀውስ ጥያቄ መልሱ
አዝማች · Chorus
ፍቅር አይደለም ዎይ ያገናኘን (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ኢየሱስ አይደለም ዎይ ያገናኘን
ጌታ አይደለም ዎይ ያሰባሰበን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ