ዝጋብኝ
Zegabegn
2013 · ትራክ 14 · 5:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል
የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል
አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ
በአንተ ልኑር አልሁን በራሴ
ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል
የአንተን ጥሎ በራሱ ይሮጣል
አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ
ደርሶ አሳቢ ስሆን ለራሴ
አዝማች · Chorus
እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ
እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈቃድህ በልቤ ላይ ትሁን
ትሰረኝ በራሴም አልሁን
ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ
አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ
ጥላህ ስር በምቾት አድራለሁ
ዘመኔን በአንተ ስር ከአደረከው (፪x)
የተከፈተ በር ሁሉ ከአንተ አይደለም
ነግ ሊያጐድለኝ እንጂ ለመልካም አይደለም
ተደባሎቆ የገባን ስኬቴን አውጣልኝ ከቤቴ ከቤቴ
ሁሉ የሞላበት የሃሰት ገነት ምን ሊበጅ ያለአንተ አንተ የለህበት
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሻለኛል ያንተው በረሃ
በላይ እህል ውኃ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ዝጋብኝ የስኬቴን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን እዳ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
ይቅርብኝ የምቾቴን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን ቁጣ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
አዝማች · Chorus
እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ
እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የአንተን ውድ ጊዜ መጠበቅ አቅቶኝ
የልብህን ሃሳብ መታገስ ተስኖኝ
የፈጠንኩ ሲመስለኝ ዘግይቼ
እንዳልገኝ ከአየኸው ወርጄ
የእንጀራ ጩኸቴ ጽኑ ልመናዬ
በሞላልኝ ማግስት እንዳይሆን ገዳዬ
አንተ ያልከው ይሁን በሕይወቴ
እኔ አልቅደም ቅደመኝ አባቴ
ቁጥር 6 · Verse 6
ዝጋብኝ የስኬቴን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን እዳ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
ይቅርብኝ የምቾቴን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን ቁጣ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ
እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ