Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በፀሎት

Betselot

2013 · ትራክ 7 · 4:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰውማ የእራሱ ችግር በዝቶበት፥

ያዋየዋል ለጠናበት፤

ለእራሱ መሆን አቅቶት፥

ጭንቀት ሰፎት፤

ማን ሊረዳው ማን አቤት ብሎት

ውይ ሰው አልኩኝ እኔም በችግሬ

ሁሉም ሲሰወር ከሰፈሬ

አለሁ ያለኝ በደህና : ቀን

ውሉ ጠፋብኝ በከፋኝ ቀን

ዘወር ስል ከሰውም ከእራሴ

ጌታ ነው ለካ መልሴ

በይ ፀሎቴ (፪x)

ዛሬ አገናኚኝ ቶሎ ከአባቴ

ባለቅስ ተደፍቼ እግሩ ሥር ወድቄ

ስነሳ ፊቴ በርቶ ልቤ በእርሱ ረክቶ

ቢመለስም ባይመለስም ጥያቄው

ውስጤ ሰላም ነው

ከእኔ በላይ የሚያስብልኝ እርሱ አዋቂ ነው

ብቻ አልሰወር አልጥፋ እንጂ እኔ ከሥሩ

እንኳን ነገሬን እኔ አልፈዋለሁ ሙሉ ዘመኑን

(በፀሎት)

መልስ ይመለሳል በፀሎት

ልብ ይጠበቃል በፀሎት

በፀሎት በመንበርከክ (፪x)

ቅርብ ነው አጠገቤ ነው ጌታዬ

የእኔ የሚለኝ ወዳጄ

ታዲያ 'ለማን?' 'ለምን?' ብዬ እጨነቃለሁ

ልመናዬን አስታውቃለሁ

አእምሮን የሚያልፍ የአምላክ ሰላም

ልቤን ሃሳቤን ይጠብቃል

ደስ ይለኛል በእርሱ ሁልጊዜ

ላይቀር ያለልኝ ባለው ጊዜ

ሲገባኝ እውነቱ ለእራሴ

ጌታ ነው ለካ መልሴ

በይ ፀሎቴ (፪x)

ዛሬ አገናኚኝ ቶሎ ከአባቴ

ባለቅስ ተደፍቼ እግሩ ሥር ወድቄ

ስነሳ ፊቴ በርቶ ልቤ በእርሱ ረክቶ

ቢመለስም ባይመለስም ጥያቄው

ውስጤ ሰላም ነው

ከእኔ በላይ የሚያስብልኝ እርሱ አዋቂ ነው

ብቻ አልሰወር አልጥፋ እንጂ እኔ ከሥሩ

እንኳን ነገሬን እኔ አልፈዋለሁ ሙሉ ዘመኑን

(በፀሎት)

መልስ ይመለሳል በፀሎት

ልብ ይጠበቃል በፀሎት

በፀሎት በመንበርከክ (፪x)

በፀሎት በፀሎት በፀሎት (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ